Duration 14:37

በሀላባ ዞን የህዝቡን የፍትህ ጥማት ለማርካት የፍትህ አመራሩ ሚና የጎላ መሆኑ የዞኑ ዓቃቤ ህገ መምሪያ ገልፀዋል።

Published 1 Sep 2021

ነሐሴ 24/2013 ዓ.ም ፣ሀላባ ቁሊቶ በዞኑ የሚገኙ የፍትህ ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ የህዝቡን የፍትህ ጥማት ለማርካት የፍትህ አመራሩ ሚና የጎላ መሆኑን የሀላባ ዞን ዓቃቤ ህገ መምሪያ ገለፀ። መምሪያው በዞኑ በየደረጃው ከሚገኙ የፍትህ አመራሮች ጋር በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የውይይት መድረክም አከናውኗል። በዚህ ወቅት በሀላባ ዞን ዓቃቤ ህግ መምሪያ ኃላፊ በአቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሳ እንደገለፁት በዞኑ የሚገኙ የፍትህ ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ የህዝቡን የፍትህ ጥማት ለማርካት የፍትህ አመራሩ ሚና የጎላ ነው። በተለይም በዞኑ ያሉ የፍትህ ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለቅሞ በመያዝና በማረም ከማስከተል አንጻር የፍትህ አመራሩ በባለቤትነት መስራት እንደሚገባ አቶ አብዲልቃድር አሳስቧል። የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በፍትሕ መዋቅር አገልግሎት አሉ ያሏቸውን ጉድለቶች በዝርዝር በማንሳት በቀጣይ ችግሮቹን ከምንጫቸው ለማክሰም ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የህብረተሰቡን የፍትህ እጦት በማስቀረት የተሸለ አገልግሎት ለማስፈን ተግተው እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

Category

Show more

Comments - 0